የጾታ ግንኙነት (ወሲብ) በሕይወታችን ውስጥ የሚጫወተው ሚና
ወሲባዊ ነፃነት እና ወሲባዊ እርካታ ከጥንቃቄ እና ደህንነት ጋር ልናራምደው የሚገባ ነው።
መግቢያ
ወሲብ የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት ከሚባሉት መጠጥ ልብስ እና ቤት ጋር እኩል የሚጠራ ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅ ለማንነቱ አስፈላጊ ክፍል ነው። ወሲብ ስለ አካላዊ እርካታ ብቻ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን ብዬ አስባለው ከሌላ ሰው ጋር ስለሚኖር ጥምረት ፣ ማንነታችንን የምንገልፅበት ስሜታዊ መንፈሳዊ እና እውቀታዊ ተግባር ነው።
ለኤልጃቢቲኪው+ ለሆንን ሰዎች በመካከላችን ስላሉ ወሲባዊ ግንኙነቶች የጥላቻ እና የኩነኔ እንዲሁም የትችት ምክንያት የመጠላታችን የመገፋታችን ምክንያት ነው። ጠለቅ ብለን ካየነው የማህበረሰቡ የእውቀት ማነስ ሁለት ተመሳሳይ ሰዎች (ለምሳሌ ወንዶች) እንዴት ሊዋሰቡ ይችላሉ የሚል አካላዊ መዋቅር መመሳሰል ላይ የተመሰረተ ጥላቻ ያራምዳሉ እኔ እስከሰማውት እና እስካየውት ስለ መፋቀር አለመቻል የሚያነሳ የለም ይልቅ ወሲብ እንዴት እንደሚደረግ እና የሚደረግበትም መንገድ ኢተፈጥሯዊ እንደሆነ መናገር ነው።
ለዜጋ(LGBTQ2+) ሰዎች መሰረታዊ ፍላጎት የሆነው አንዱ ክፍል ከልጅነት ጀምሮ በማጠልሸት እና ሰለራሳችን ወሲባዊ ፍላጎት እና ጥማት የተነገረን ውሸት ለወሲብ ህይወታችን ከፍተኛ መሰናክል ሆኗል ለወሲብ የሚኖረንንም ምልከታ የለወጠ ብቻ ሳይሆን ወሲብን ከትክክለኛው ምንነቱ ውጪ በመጠቀም እራሳችንን በባዶ ማለቂያ የሌለው ዙረት ውስጥ እንድንከት ምክንያት ሆኗል።
ወሲብን ከባዮሎጂል ፣ ሳይኮሎጂካል እና ማህበራዊ እይታ አንፃር መቃኘት የተጫነብንን ቀንበር ለመስበር ይጠቅመናል። የተፈጥሮ አንዱ ክፍል እንደመሆኑ እውነታውን መቀበል እና ለተሻለ የወሲባዊ ግንኙነት እንድንመራ አቅም ይሰጠናል። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ኮሚኒቲ እንደመሆናችን ያለንበትን ሁኔታ መመልከት እና እውነታውን መጋፈጥ አለብን ወሲባዊ ግንኙነቶች ለተለያኑ ህመሞች በሽታዎች ሊዳርጉን ሊረዳን የሚችል አለመኖሩን መረዳት እና በህጉ መሰረት ወንጀለኞች መሆናችን ስጋታችንን እንደሚጨምረው መረዳት አለብን ከዛ በላይ የመጋለጥ እና ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ እና ከላላ የለሽ መሆናችንን ማወቅ አለብን።
ወሲብ ምንድነው ?
#ባዮሎጂካሊ በርካታ ቀጦች ወሲብን ከመዋለድ ጋራ አገናኝተውቴ የኩዊር ወሲባዊ ግንኙነት ልጅ ስለማይፈጥር ኃጢአት ነው ይሉናል ነገር ግን በወሲብ ወቅት የሚለቀቅ እንደ ዶፓሚን፣ ኢንዶርፊን ፣ ኦክሲቶሲን በሁለቱ ተዋሳቢዎች መካከል የመተሳሰር እና የአንድነትን ስሜት እንደሚፈጥር ያሳየናል። አንዳንዶች በዚ ጉዳይ የወሲብ አጋራቻችን ስሜት ሁሉ ሳይነግሩን ለመረዳት የምንችልበትን አቅም እንደሚፈጥር ይናገራሉ። እንደ ሩቅ ምስራቅ ሀገራት ሀይማኖታዊ ፍልስፍና ካየነው በሁለቱ ተዋሳቢዎች መካከል ለ10-12 አመታት የሚቆይ (በአንድ የወሲብ ግንኘነት ) Astral cord እንደሚፈጠረ እና የዛን ሰው አካላዊ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ሁናቴ ሁሉ ሳይቀር እንደምንቀበል እና ለ12አመታት እንደምንሸከም ይናገራሉ።
#ሳይኮሎጂካሊ ካየነው ወሲብ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከሚኖሩን ግንኙነቶች የለጠ ግላዊ እና የተሟላ የተገለጠ ህብረት የምንፈጥርበት ነው እርቃን የምንሆነው አካላችንን ብቻ አይደለም ነገር ግን ውስጣችንንን ጭምር ነው የመታየት ፣ መወደድን የመቀበል ፣ የመፈለግን ተፈጥሮአዊ ጥማት የሚያረካ ነው። በወሲብ ሀፍረታችን ጭንቀታችን እንዲሁም ፍርሃታችንን ሁሉ ሳይቀር ልንገልፅበት እንችላለን። በታንትሪክ ፍልስፍና ወሲብ አካላዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ተግባር ነው ሰው በንቃት ራሱን እና ወሲባዊ ጥማቱን መመልከት ከቻለ ስለማንነቱ እና ስለ እውነተኛ መልኩ መረዳት እንደሚችል ያስተምራሉ ።ታንትራ ወሲብን የሚመለከተው ንቃተ ህሊናን የምናሰፋበት እና በጥልቀት የምናድግበት መንገድ እንደሆነ ነው። ስለ መራባት ወይም ስለመዋለድ ብቻ አይደለም።
#ከማህበራዊ ህይወት አንፃር ካየነው ማህበረሰብ የተገነባው ከቤተሰብ ነው ቤተሰብ ደግሞ በመዋለድ ላይ የተመሰረተ ነው የሚል እንደ እኛ ሀገር ባሉ ሀገራት አመለካከት የኩዊር ወሲብ ይህን የቤተሰብ መሰረት የሚያፈርስ ነው ትልቁ ነገር ግን ቤተሰብ የተመሰረተው በመዋለድ ላይ አለመሆኑ ነው ይልቅ በፍቅር ላይ እንደሆነ ነው። በተለያዩ ብሔሮች በኢትዮጵያም ሳይቀር ከሴት እና ከወንድ ወሲብ ውጪ ስላሉ ወሲባዊ እውነታዎች የተዘገቡ አሉ። ቀጥነትን ዋና ለማድረግ በተመሰረተ ማህበረሰባዊ ዶግማ የኩዊርን ወሲባዊ ግንኙነት መካድ እና ለመሻር መጣር የኩዊር ስዎችን ህልውና መድመሰስ ነው። እንደ ኩዊር የማህበረሰቡ ክፍል ግን ይህ ጥላቻ መሰረቱ አለማወቅ እና ጭፍንነተኝነት እንደሆነ በመገንዘብ የራሳችንን እውነት መቀበል መቻል አንድ የተቃውሞ እና የልዕልና ማሳያ ነው።
ወሲብን ለምንድነው የምንፈልገው ?
ወሲብ ቅዱስ ነው ይህን መገንዘብ አለብን። ሰው በተፈጥሮው የመወዳጀት እና መታየት የመፈለግ ስሜት እና ጥማት በውስጡ አለ ከዛ በላይ ባዮሎጂካሊ ቅንዝርና (Libido the natural sexual desire people have) ስላለው ይህን ቅንዝርና በወሲብ መልክ የማውጣት የማቅለል ውስጣዊ ግፊት ይኖረዋል።
ባዮሎጂካሊ ወሲብ ውጥረትን የመቀነስ በሽታ የመከላለከል አቅምን የመጨመር እንዲሁም የእንቅልፍ ሁኔታን የማስተካከል ስሜታዊ ሚዛናዊንን የመጨመር አቅም አለው አካላችን ደግሞ የሚጠቅመንን ነገር እንድናደርግ ይገፋናል።
ሳይኮሎጂካሊ ወሲብ በራስ መተማምንን እራስን የመቀበልን እንዲሁም ግንኙነት (Intimacy) የመጨመር አቅም ስላለው ከወሲብ የምናገኘውን ነገር እንፈልጋለን በሚያሳዝን ሁኔታ ወሲብ ይሰጠናል ያልናቸውን ነገሮችን በተቃራኒ አሉታዊ ተፅዕኖ የመከሰት አቅም አለው። ምክንያቱም ሺ ጊዜ ወሲባዊ ተግባር በማድረግ ራስን መቀበል ወይም መውደድ አይመጣም ወሲብ የበለጠ ራሳችንን እንድንረዳ አቅም ይሰጠናል እንጂ ለራስ ጠልነት (Internalized homophobia) ፈውስ አይደለም።
ወሲባዊ እርካታ እጦት ምክንያት
#ስለወሲብ ያለ ውስጣዊ ሀፍረት : ኢትዮጵያዊ እንደመሆናችን ስለ ወሲብ ስንሰማ ያደግነው የሚያሳፍር ሊወራ የማይገባዉ የሚታፈርበት ነገር ነው ይህ ደግሞ ስለ ወሲብ የሚኖረንን ውስጣዊ እይታ ያጠለሸዋል። እንደ ዜጋ ስንመለከተው ደግሞ ቀጡ ሊኖረው ከሚገባ ሀፍረት በእጥፍ በመካከላችን የሚኖረው ሀፍረት ይጠነክራል ስለ ውስጣዊ ጥማታችን መሸማቀቅ "ባለጌ" "ስርአት አልበኛ" "ጋጠወጥ " የመባሉ ስሜት ፍርሃት ከወሲብ አጋራችን ጋራም ጭምር ሊከሰት ይችላል። የወሲብ ጥማታችን እና ፍላጎታችንን በማፈን ከእውነተኛ ህብረት (intimacy, connection) እንዳናደርግ ይከለክለናል። የታንትራ ፍልስፍና የሚነግረን ወሲባዊ ግንኙነት በነፃነት ሊደረግ እንደሚገባው ነው ካማሱትራ የተበላ ጥንታዊ የወሲብ ፣ የህብረት ፣የጥምረት ፍልስፍና (ባጭሩ ፓዚሽን የመጡበት ፍልስፍና ነው ካማ=እርካታ ሲሆን ሱትራ = መመሪያ ማለት ነው) ወሲብ ላይ ሀፍረት ካለ ወሲቡ ተፈጥሮአዊ ምንነቱን ያጣል ይለናል
#አካላዊ ሀፍረት ስለራሳችን ሰውነት የሚኖረን ምልከታ ወሲብ ላይ በሚኖረን እርካታ ላይ ከፍተኛ ተፅፅኖ ያሳድራል። 'አላምርም' 'ወፍራም ነኝ' 'በጣም ቀጭን ነኝ' 'ጠቆርኩ ''አስቀያሚ ነኝ' 'ቁላዬ ትንሽ ነው' ወዘተረፈ እና ሌሎች ስለ ሰውነታችን የሚኖረው ምልከታ ወሲብ ላይ እንዳንደሰት ምክንያት ተደርጎ ሊቀርብ ይችላል። ስለ አካላዊ ማሸማቀቅ ያዘጋጀነውን እዚ ላይ ማንበብ ይቻላል!
#Hook-up ባህል በዜጋው ዘንድ ባህል የሆነና በርካቶች የሚኮንኑት (የሚገርመው የኮነነውም ባህሉን የምናጠነክር ነው) ሁካፕ ማድረግን እየኮነንኩ ወይም እየተቸው አይደለም ነገር ግን ይህ የሁካፕ ተግባር የሚፈጥረውን ተፅዕኖ መረዳት ያሻናል እንጂ ከላይ እንደጠቀስኩት ባዮሎጂካሊ ጥምረት እንዲኖሩ እንደሚረዳን ያየናቸው ሆርሞኖች በወሲብ ግንኙነት ወቅት ይለቀቃሉ በሰውነታችን ውስጥ በተደጋጋሚ የምናገደርገው ወሲባዊ ግንኙነትና ከአንድ ሰው ጋር የዘለቀ እና የሚቆይ ህብረትን ለማስጠበቅ እንዳንችል ተፅዕኖ ያሳድርብናል። ሌላው ወሲብን ጊዜያዊ እርካታ ላይ ብቻ ማጥበብ ከጀርባ ስላለን አመለካከት እንድንቃኝ ሊያስገድደን ይገባል። ኢትዮጵያ ሆነን መጋባት የለም ብለን ስለሰብን ማንነታችንን በጊዜያዊ እርካታ ብቻ ለማርካት እና ነገ ወጣለሁ የሚል አለመካከት በበርካቶች ዘንድ ሊኖር ይችላል።
በሀይማኖት ተቋሞ ወይም በህግ ፊት ስላልተጋባን አንዳችን ለሌላችን ቃል ኪዳን መግባት አንችልም ማለት አይደለም።
#የመነጋገር እጥረት : ከወሲብ በፊት ስለ ወሲባዊ ፍላጎቶቻችን (ሮል ኤጅ ከማለት የጠለቀ) ለማውራት ላይ ስንቶቻችን ነን ፍቃደኛ ? ከወሲብስ በኋላ ስለ ወሲቡ የማውራት ልምድ ስንትቻችን አለን? ወሲብ ላይ መነጋገር አንዱ አካል ለሌኛውን አካል መረዳት እንዲችል ያግዘዋል። ወሲባዊ ተግባር ግላዊ እርካታን ስለማግኘት አይደለም ይልቅ ለወሲብ አጋራችን እርካታ ራሳችንን መስጠት እሱም ለእኛ እርካታ ራሱን መስጠት እንጂ። መነጋገር እና መወያየት የበለጠ ጤነኛ፣እርካታ ያለው ህመም የሌለው ወሲባዊ ልምድ እንዲኖረን እና ከወሲባዊ ትራውማ ራሳችንን እንድንጠብቅ አቅም ይሰጠናል።
#ስለማንነታችን የሚኖረን ምልከታ : ወሲብ ፍቅርን የምንገልፅበት መሳሪያ ነው ለብቻው ባዶ አካላዊ ፍትጊያ ነው የሚሆነው ለወሲቡ ትርጉሙ ምንድነው የሚለውን መረዳት ከውስበት በኋላ የሚኖረንን ስሜት ይወስነዋል። እርካታን ብቻ ፈልገን ከተገናኘን ከምናደርገው ወሲብ ህብረትን መወደድን ወይም ፍቅርን መፈለግ ራስን ማቁሰል ነው። ነገ የለውም ህይወቴ በሚል የሚደረጉ ወሲባዊ ግንኙነቶች ባዶ አዶርገው ይለቁናል። እርግነጠኛ ነኝ ከምናፈቅረው ሰው ጋር የምናደርገው ወሲብ እና እንዲሁ ለቅንዝርና ምላሽ ብቻ የሚደረግ ወሲብ ያለውን የእርካታ ልዩነት መረዳት አይከብደንም
#እኩል አለመጨረስ ወንዶችን እንደምሳሌ ብለወስድ ቶፕ የሆነው የራሱን እርካታ ካስቀደመ የአጋሩን እርካታ የመጠበቅ እይታ አይኖረውም ወሲብ ላይ ስንሆን እንድናስተውል የሚገባዊ በሰአቱ ያለብን ብቸኛ ሃላፊነት ደህንነታችንን በማያወላዳ መልኩ የአጋራችንን እርካታ ማስቀደም ነው። አብሮ መጨረስ ከወሲብ በኋላ የሚኖረንን ስሜት ይወስነዋል። ከፍተኛ የፍቺ ምክንያት ተብሎ ከሚጠቀሱ ነገሮች አንዱ ወሲባዊ አለመጣጣም ነው ይህም አንዱ እየረካ ሌላው ሳይረካ መቆየትን ያሳያል። ከዚህ ቀድም ስለ በቶሎ መጨረስ የተነጋገርነውን መምለክትም ያስፈልጋል ችግሮችን ማውራት እና መነጋገር ለተሻለ ወሲባዊ እርካታ ግብአት ነው።
ደህንነት እና ወሲባዊ ግንኙነት
የአባላዘር በሽታ ከመከላከል የቶፕ የቦተም የሚባል ተግባር አይደለም የሁላችንም ነው
ለቶፕ ሮል ወሳጅየቀረበ ጥቂት ምክረ ሀሳብ
ሁሌ ኮንዶሞ መጠቀም ግዴታ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል በመላጣው የበለጠ ደስ ይለኛል ተብሎ ጤንነታችንን አደጋ ላይ መጣል የለብንም
ጌሾ ወቀጣ ይመስል ችኮላ እና ከአቅም በላይ የሆነ ኃይል መጠቀም ወይም መግፋት አያስፈልግም አጋራችንን በመጠየቅ እንቅስቃሴውን በተቻለ መጠን ረጋ ያለ እንዲሆን እንጣር ታንትራ እንደሚለው ከሆነ ችኮላ ትክክለኛ የወሲብን እርካታ ያሳጣል ይላል።
ሉብሪካንት እንደ ልብ ማግኘት ሆነ ለመግዛት አቅርቦት የሌለብ ቦታ እንደመሆናችን መጠንቀቅ እና የአጋራችንን ደህንነት እና ስሜት መጠበቅ ያስፈልጋል
ንፅህናን መጠበቅ must ነው
ለቦተም ሮል ወሳጅ የቀረበ ምክረ ሀሳብ
ገና ለገና ኮንዶም መያዝ ያለበት ቶፕ ነው በሚል የራስን ኃላፊነት መተው ቂልነት ነው ሁሌ ኮንዶም አይለየን ከፍቅር አጋራችንም ጋራ ቢሆንም።
ቅድመ ወሲብ ዝግጅት እንደ ዱሺንግ ወይም ፊንገሪንግ በሚደረግበት ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በወሲብ ጊዜ የሚፈጠር ነገር እንዳያሸማቅቅን አስቀድመን ንፅህናን በመጠበቅ መጠንቀቅ ከተፈጠረም ተፈጥሮዊ የአካላችን ክፍል እንደመሆኑ በመገንዘብ አግባብነት የሌለውን መሸማቀቅ ሆነ ማሸማቀቅ (ከቶፓች) መኖር አይጠበቅበትም።
እንጀራ ከተመገብን በኋላ ወሲባዊ ግንኙንት ከማድረጋችን በፊት 2-4 ሰዓት መጠበቅ እንዳለብን ይመከራል። የፊንጢጣን ውጫዊ ክፍል በደንብ ማፅዳት እና ሁሌ የሰውነታችንን ንፅህና መጠበቅ ይመከራል። ዱሽ(ውስጣዊ የፊንጢጣ ክፍል ማፅዳት) ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ካሉ ከፍተኛ ፅዳት እና ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
በውሃ በቀላሉ ሊወገድ የሚችሉ ማለስለሻዎች በአቅራቢያችን በነፃነት ስላሌሉ በቻልነው መጠን መጠንቀቅ ይመከራል ከዚ ቀደም የፊንጢጣ መቀደድ የተጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ነው። Water based ማለስለሻ ለመተካት አስቸጋሪ ቢሆንም አፋችን ንፁህ ከሆነ ምራቅ መጠቀም፣ የኮከናት ቅባቶች ወይም ከኬሚካል ንፁህ የሆኑ ኦሊቬራ ቅባት መጠቀም ይቻላል። እንደ ቫዝሊን ያሉ ፔትሮሊየም አዘል የሆኑ ቅባቶች ጉዳት ስለሚያስከትሉ መጠቀም የተከለከለ ነው።
በየጊዜው የአባላዘር በሽታ ምርመራ ማድረግ ለሁሉም ይመከራል
ለሳይድ
ለሳይድ የሚደረጉ ወሲባዊ ግንኙነቶች የአባላዘር በሽታ ተጋላጭነት ይቀንሳል በሚል ጥንቃቄ ማጉደል አያስለፈልግም ሁሌ ለደህንነታችን ጥንቃቄ ማስቀደም አለብን።
ወሲባዊ ግንኘነት ለማድረግ በሚደረግ መገናኘት አካላዊ ደህንነት መጠበቅ
ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መሆናችንን እና በየጊዜው ከምንሰማው ችግሮች እና ክስተቶችን (የበለጠ ደግሞ አሁን በቀጦች ዘንድ እየተደረገ ያለው የጥላቻ ዘመቻ ) ከፍተኛ ጥንቃቄ እና በንቃት ራሳችንን መጠበቅ እንዳለብን ልንረዳ የሚገባበት ጊዜ ላይ ነን!
በመጀመሪያ ሰው ለማግኘት በምናደርገው እንቅስቃሴ ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀማችን ግድ ነው የምንጠቀማቸውን አፕልኬሽን የደህንነት መጠበቂያ በሙሉ መጠቀም መቻል አለብን። ግላዊ መረጃችንን ፣ፍቶዎቸ ወይም መኖሪያ አድራሻ ሆነ ሌላ ወደኛ የሚጠቁሙ ነገሮችን በጭራሽ አለመጠቀም ልምዳችን ልናደርገው ይገባል። የዲጂታል አለም ደህንነታችንን መጠበቅ መማር አለብን።
ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ የምናገኝ ከሆነ ህዝብ የሚበዛበት ቦታ መምረጥ እና መጥፎ ነገር ቢከሰት በማለቴ እንዴት ራሳችንን ከዛ ሁኔታ እንደምናርቅ በልባችን መዘጋጀት (ምንም እንኳ አሁን የማናቀውም አዲስ ሰው መገናኘት ባይደገፍም ማለት ነው)
አዲስ ሰው ከማግኘታችን በፊት ስለዛ ሰው ከሌሎች ኩዊር ሰዎች ማጣራት
የምንሄድበትን ቦታ ለምናምነው ጓደኛ ማሳወቅ ለምናገኘውም ሰው ከልክ ያለፈ ግላዊ መረጃ ከመስጠት መጠበቅ
ሰው ለማግኘት ከተማ አቋርጦ መሄድ የአደጋ ተጋላጭነታችንን የሚጨምር በመሆኑ የበለጠ ማሰብ እና ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል
ከተማመንን በኋላ ቤታችን ሰው የምናመጣ ከሆነ በርካታ ጊዜ እንደሰማነው እቃ ሰርቆ መውጣት ሊከሰት ስለሚችል ጠንቃቃ መሆን እና ግላዊ መረጃ የሚሆኑ አንዳንድ ነገሮችን ከፊት ማሸሽ ይመከራል። (አሁን ካለው ነገር የተነሳ ግንኙነታትንን ማጥበብ እና ከምናቃቸው ጋራ ብቻ መገናኘት ይመከራል )
እና ሌሎች ይጠቅሙናል የምንላቸውን ነገሮች መተግበር አለብን። ከሁሉ በላይ ወሲብ ማድረግ ስህተት ባይሆንም ለወሲብ ብቻ ማደርም ውስጣዊ ሌላ ችግር ጠቋሚ ስለሚሆን ራስን ረጋ ብሎ መቃኘት ያስፈልጋል።
ወሲባዊ ነፃነት እና ወሲባዊ እርካታ ከጥንቃቄ እና ደህንነት ጋር ልናራምደው የሚገባ ነው።



